ተልዕኮ
ከተለያዩ ለጋሽ አካላትና ከኢንቨስትመንት ሃብት በማሰባሰብና መልሶ ስትራቴጂክ በሆኑና የገበያ ጉድለት በሚታይባቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ በማሰማራት የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማምጣትና በማህበራዊ የልማት መስኮች በመሳተፍ ለክልሉ ህዝብ የኑሮ ደረጃ መሻሻል እገዛ ማድረግ፡፡
ረዕይ
እ.ኤ.አ በ2030 በክልሉ ቀዳሚ የበጎ አድራጎትና የልማት አጋር ተቋም ሆኖ ማየት፡፡
ጋፋት ኢንዶውመንት በክልሉ ፍትህ ቢሮ መንግስታዊ ባልሆነ ዘላቂ የበጎ አድራጎት ድርጅትነት ጥር 22 ቀን 2000 ዓ.ም እውቅና አግኝቶ ተቋቋመ፡፡ ኢንዶውመንቱ ሲቋቋም በዋነኝነት ሁለት ተልዕኮወችን አንግቦ ነው፡፡የመጀመሪያው ከኢንቨስትመንት የሚያገኘዉን ሀብት ለበጎ አድራጐት ሥራዎች በማዋል የክልሉን የልማት እንቅስቃሴ ማገዝና ለህዝብ ኑሮ መሻሻል የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከኢንቨስትመንት መስኮች የሚገኘውን ትርፍ መልሶ ስትራቴጂክ በሆኑ ዘርፎች ላይ ኢንቨስት በማድረግ በክልሉ ውስጥ የሥራ እድልን መፍጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማምጣት ነው፡፡