Print

ላሊበላ የጥናት፣ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር

website:www.lalibeladesign.com

ተልዕኮ

በምህንድስና ዘርፍ በመጠጥ ውሃ፣መስኖ፣ህንጻ እና መንገድ እንዲሁም በንግድና ኢንቨስትመንት የጥናት፣ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ተሳትፎውን በማሳደግ ውጤታማና በስነ-ምግባርና በክህሎት የተካነ አመራርና ሰራተኛ ሃይል በማቀናጀትና ለጋራ ራዕይ በማሰለፍ በጥራትና በብቃት የማማከር አገልግሎት በመስጠት፣ዘመናዊ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና አሰራር በጥናት፣ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች የማላመድ፤የዘርፉን ጥናትና ምርምር የመደገፍና የማበረታታት ተልጭኮ ይዞ ይሰራል፡፡

ራዕይ

በምህንድስና፣በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ በጥናት፣ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ደረጃ በጥራት እና በብቃት ተወዳዳሪና ተመራጭ ኩባንያ እ.ኤ.አ.በ2030 ተፈጥሮ ማየት፡፡

በብቁ ባለሙያዎች ጥራት ያለው፣ በፈጠራ ላይ የተመሰረተና ቀልጣፋ የምህንድስና አገልግሎት በታማኝነት የመስጠት መርህን አንግቦ በ 2008 ዓ.ም የተመሰረተው ላሊበላ የጥናት፣ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ሌላኛው የጋፋት ኢንዶውመንት ኩባንያ ነው፡፡

ኩባንያው በውሃ፣በመንገድና ህንጻ ስራዎች ዘርፍ የጥናት፣ዲዛይንና ሱፐርቪዥን አገልግሎት፤በንግድና ኢንቨስትመንት የጥናትና የማማከር እንዲሁም የአከባቢ ተጽእኖ ግምገማና ጥናት አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡

እነዚህን አገልግሎቶች በጥራትና በቅልጥፍና እሰጠ የሚገኝ ሲሆን ባለፉት ሁለት አመታትም 45 የጥናትና የዲዛይን ስራዎች አከናውኗል፡፡ በተጨማሪ ወደ 70 ለሚደርሱ ግንባታዎች የማማከርና የቁጥጥር ተግባራትንም እንዲሁ፡፡በእነዚህም በደንበኞቹ ዘንድ ያስመሰገነውን ጥራት ያለው ተግባር አከናውኗል፡፡

ከዚህም የተነሳ በ 2018 በጀት አመትም የ 42 የተለያዩ ፕሮጀክቶች የጥናትና ዲዛይን ስራ ሰርቷል፡፡በቁጥጥር ዘርፍም 46 ህንጻዎችን፣10የመስኖ ድሬኔጆችን እና 22 የመጠጥ ውኃ ስራዎችን ሱፐርቪዥን አከናውኗል፡፡አንድ የአከባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ማካሄድም እንዲሁ፡፡

ላሊበላ የጥ/ዲ/ቁ ስራዎች  አሁን የሚገኝበት ነባራዊ ሁኔታ

ተ.ቁ

መገለጫ

አሁን የሚገኝበት        ደረጃ(እኤአ2018 ግማሽ አመት ድረስ)

1

የካፒታል መጠን

12.6 ሚሊየን

2

የሰው ሃይል ብዛት

ቋሚ

82

ኮንትራት

19