Print

መቅደላ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ተልዕኮ

በአማራ ክልል ብሎም በሀገሪቱ ውስጥ በሚካሄዱ የመንገድ፤የድልድይ እና የህንጻ ግንባታ ስራዎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አዋጭነት ያለው እና የአከባቢ ደህንነትን ባገናዘበ ሁኔታ በመገንባት ቀጣይነት ያለው ተሳትፎ ማድረግ፡፡

ራዕይ

እ.ኤ.አ.በ2030 በመንገድ፣በድልድይ እና በህንጻ ግንባታ ዘርፍ በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ አርኪና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ብቁ፣ተወዳዳሪና ተመራጭ ኩባንያ ሆኖ ማየት፡፡

ጋፋት ኢንዶውመንት በአማራ ክልል ከአበባ፣አትክልትና ፍራፍሬ ማምረትና ወደ ውጪ መላክ እንዲሁም ከውኃ ስራዎች ግንባታና ጉድጓድ ቁፋሮ ስራ ዘርፍ ባሻገር በመሰረተ ልማት ግንባታ ዘርፍም የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት በ 2004 ዓ.ም መቅደላ ኮንስትራክሽን በሚል ስያሜ ኩባንያ አቋቁሞ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ኩባንያው "ታማኝነት፣ጥራትና ቅልጥፍናን "መርሁ በማድረግ በዋነኛነት በመንገድና በድልድይ ግንባታ እንዲሁም በህንጻ ስራዎች የተሰማራ ሲሆን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሸከርካሪዎችንም የማከራየት አገልግሎት ይሰጣል፡፡

በዚህም ባለፉት ስድስት አመታት አራት ድልድዮችን፣ ሁለት ከፍተኛ ህንጻዎችን እንዲሁም 23 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ በጥራት ገንብቶ አስረክቧል፡፡በ2018 በጀት አመትም የ16 የድልድይና ህንጻ ፕሮጀክቶች ግንባታ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ኩባንያው በተለይ በክልሉ ለስራ አስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎችና አከባቢዎች ጭምር ገብቶ በመስራት የክልሉን ልማት ከማገዝ ባሻገር የህዝብ አለኝታነቱን እያረጋገጠ የሚገኝ ኩባንያ ነው፡፡

ኩባንያው በተለያዩ አከባቢዎች በሚያከናውናቸው የግንባታ ስራዎች ልክ እንደሌሎቹ የጋፋት ኢንዶውመንት ኩባንያዎች ለበርካታ ስራ አጥ ወገኖች የስራ እድል በመፍጠሩ ሂደትም ጉልህ ድርሻ አበርክቷል፡፡አሁንም በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡

መቅደላ ኮንስትራክሽን አሁን የሚገኝበት ነባራዊ ሁኔታ

ተ.ቁ

መገለጫ

አሁን የሚገኝበት        ደረጃ(እኤአ2018ግማሽ አመት ድረስ)

1

የካፒታል መጠን

21 ሚሊየን

2

የሰው ሃይል ብዛት

ቋሚ

52

ኮንትራት

87

3

የማሽነሪ ብዛት

11