Print

ስ እሳት ውኃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ተልዕኮ

ተወዳዳሪ አዋጭ በሆነ ወጪ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ፣ውሃ አቅርቦት፣የመስኖ፣ፕሮጀክቶችንና የውሃ መጠን ፍተሻ ስራዎችንበጥራት በመስራት የደንበኞችን እርካታ ማረጋገጥ፡፡

ራዕይ

በ2020 ዓ.ም በሀገራችን ተወዳዳሪና ብቃት ያለው የውሃ ስራዎች ተቋም ሆኖ ማየት፡፡

የጋፋት ኢንዶውመንት ሌላኛው ኩባንያ ነው፡፡ጢስ እሳት ውኃ ስራዎች፡፡ ኩባንያው "ጥራት፣ታማኝነትና ተመጣጣኝ ዋጋ"የሚል መለያ(motto) ይዞ በ 2001 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን ይህንንም በተግባር በማረጋገጡ ከተመሰረተ በጥቂት አመታት ውሰጥ በአሁኑ ወቅትበአማራ ክልል በተመሳሳይ ዘርፍ ከተሰማሩ መሰል ድርጅቶች ጋር ተወዳዳሪና ተመራጭ እየሆነ ይገኛል፡፡

ጢስ እሳት ውኃ ስራዎች በሚከተሉት የስራ ዘርፎች ማለትም፡-

እነዚህን ተግባራት ከማከናወን አንጻር ኩባንያው ባለፉት ዘጠኝ አመታት 14 የመስኖ አውታሮችን፣28 የተለያየ ደረጃ ያላቸውን የመጠጥውኃ ተቋማትን ገንብቷል፡፡በ2018 በጀት አመት ግማሽ አመት ድረስ 24 የመጠጥ እና የመስኖ አውታሮችን በመገንባት ላይ ሲሆን ስድስትአዳዲስ ግንባታዎችን ለማከናወን ውል ይዞ የቅድመ ግንባታ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፤

ኩባንያው በአሁኑ ወቅት ዘርፉ የደረሰበት የዘመናዊ ማሽነሪዎች ባለቤትና እና ይህን እና ሌሎች የዘርፉን ቴክኖሎጂዎች መተግበር በሚችልየሰው ኃይል እራሱን አደራጅቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ከሰው ሃይል አንጻርም 127 ቋሚ፣107 ኮንትራት በድምሩ 224 ሰራተኞችአሉት፡፡በዚህም ኩባንያው ለክልሉ በተሰማራበት መስክ እያበረከተ ካለው አስተዋጽኦ ባሻገር የስራ እድል በመፍጠር ረገድ የበኩሉንእያበረከተ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች አሁን የሚገኝበት ነባራዊ ሁኔታ

ተ.ቁ

 

መገለጫ

አሁን የሚገኝበት        ደረጃ(እአአ2018ግማሽ አመት ድረስ)

1

የካፒታል መጠን

76 ሚሊየን

2

የሰው ሃይል ብዛት

ቋሚ

127

ኮንትራት

107

3

የማሽነሪ ብዛት

12