Print

ጋፋት ኢንዶውመንት ባለፉት አስር አመታት የኢንዶውመንቱን ስራ አመራር ቦርድ በተለያዩ ደረጃዎች ላገለገሉ ግለሰቦች የምስጋና የሽኝት ፕሮግራም አደረገ፡፡
ፕሮግራሙን አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንዶውመንቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽመልስ በላቸው እንደተናገሩት አላማው ግለሰቦች ጋፋት ኢንዶውመንት አሁን ለደረሰበት ደረጃ ሚናቸው ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር እንዳንዶቹም ለኢንዶውመንቱ መመስራት ኃሳብ ያፈለቁ መሆናቸውን ጠቅሰው ለዚህ ተግባራቸው ከማመስገን ባሻገር በቀጣይም ባላቸው እውቀት፣ በኃሳብና አስተያየት ድጋፋቸው እንዳይለይ ለማድረግ ጭምር ነው ብለዋል፡፡
የስራ አመራር ቦርዱን በተለያየ ጊዜ ያገለገሉት ግለሰቦች፡-
1. አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
2. አቶ አለምነው መኮንን
3. አምባሳደር ውለታው ኃ/ማርያም
4. ዶ/ር አምላኩ አስረስ
5. ዶ/ር ተሾመ ዋለ
6. ዶ/ር ጌትነት አለሙ
7. አቶ ደጀኔ ምንልኩ
8. አቶ ዘመነ ፀሃይ
9. ወ/ሮ ገነት ገ/እግዚአብሄር
10. አቶ አለምነው አለልኝ ናቸው፡፡
በፐሮግራሙ ተገኝተው ሽኝት የተደረገላቸው ግለሰቦች እንደተናገሩት ይህ አይነቱ ተግባር ለሚሸኘው ብቻ ሳይሆን ለቀሪውም ለስራ የበለጠ መነሳሳትን የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑ ኢንዶውመንቱ ይህን ሊቀጥልበት እንደሚገባ በመግለጽ ሌሎች ተቋማትም ከዚህ ሊማሩ እንደሚገባም እንዲሁ፡፡

 Image may contain: 3 people, people sitting, table and indoorImage may contain: 2 people, people sitting and indoorImage may contain: 3 people, people standing, people sitting, wedding and indoorImage may contain: 2 people, people sitting and indoor